በጀት የአቅርቦት ሁሉ ምንጭ እና የአጭርና የረጅም ጊዜ ልማት ፍላጎትቶች ማሳኪያ፣ የመንግስት ገቢና ወጪ ሚዛናዊነት መቆጣጠሪያ መሳሪያና የኤኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ውሳኔዎች መሰረት መሆኑ ይታመናል፡፡ ” በጀት ከሌለ ክፍያ (ወጪ) የለም ” የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡
በጀት በአጠቃላይ የሀገርን
ትላልቅ ሞተሮች ማለትም የማህበዊ ፣ ፖሌቲካዊና ኢኮኖሚያዊ
የልማት ሥራዎችን የሚያንቀሳቅስ ትንሹ (ግን ወሳኙ) ሞተር
ነው ማለት ይቻላል፡፡በጀት ለልማት
ሲሆን ልማት ደግሞ የህዝብ ነው፡፡ለዚህም ነው የመንግስት በጀት
በከፍተኛው የመንግስት አካል (ምክር ቤት) የሚታወጀው፡፡
ስልጣንና ተግባራቸው በህግ ተወስኖ የተቋቋሙት መንግስት አካላት (አስፈጻሚው) ከመንግስት
የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካት በየተቋማቸው ማህበራዊና
ኤኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎችን ያቅዳሉ፡፡ መንግስትም ዕቅዳቸውን ገምግሞ ከማጽደቅ በተጫማሪ ለዕቅዱ ማስፈጸሚያ ተመጣጣኝ በጀት ይመድባል፡፡የሚመደበው በጀትም ከኃላፊነትና ተጠያቂነት (responsibility & accountability)
ጋር ነው፡፡ ይህም እያንዳንዱ ተቋም የተመደበለትን በጀት ህግና ሥርዓትን ተከትሎ
ለታለመለት ዓላማ በማዋል የተፈለገውን
ውጤት ማስገኘት ግዴታ እንዳለበት ያመላክታል።
መንግስት እነዚህ ተቋማት የተመደበላቸውን በጀት የፋይናንስ ህግና ሥርዓትን ጠብቀው ኢኮኖሚያዊና ብቃት ባለው ሁኔታ ተጠቅመው ያቀዱትን የልማት ሥራዎች ስለማሳካታቸው፣ በሌላ መልኩ ኃላፊነትና ተጠያቂነታቸውን ስለመወጣታቸው በገለልተኛ አካል የተረጋጠ አስተማማኝ መረጃ ማግኘት ይፈልጋል፡
ለመሆኑ ይህ ገለልተኛ አካል ማን ነው? ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አንጻር ጉዳዩ የሚመለከተው
ገለልተኛ አካል በተሻሻለው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ
ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 14(1)(ሀ) እና አንቀጽ 26(1) መሰረት ኦዲት ስራውን በገለልተኛነት የሚሰራው የአዲስ
አበባ ከተማ
ዋና ኦዲተር መ/ቤት መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ዋና ኦዲተር
መ/ቤቱ በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 77/2014
ስልጣንና ተግባሩ በህግ ተወስኖ እንደገና
ተቋቁሟል፡፡
በመሆኑም መ/ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን
ሃላፊነት ለመወጣት ሁሉአቀፍ የኦዲት ዘርፎችን ያማከለ፣ የኦዲት ጥራትና
ሽፋንን መሰረት ያደረገ፣ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የኦዲት አገልግሎት በመስጠት በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የፋይናንስ አሰራር
ግልጽነትና ተጠያቂነት ሰፍኖ መልካም አስተዳደር እንዲጎለብት የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት ያስቀመጠውን ተልዕኮ ማሳካት ይጠበቅበታል፡፡ ለዚህምእያንዳንዱ የመ/ቤቱ አመራርና ባለሙያ የተሰጠውን ህዝባዊ ኃላፊነት በታማኝነት፣ በገለልተኝነትና ሙያዊ ጥንቃቄ መወጣት ግዴታ አለበት።ኦዲት ተደራጊ ተቋማትም የተሰጣቸውን የህዝብ ሀብትና ንብረት
በአግባቡ ስለመያዛቸውና ለህዝብ ጥቅም ስለማዋላቸው እንዲረጋገጥ ኦዲተ ማስደረግ ከድርድር የሚገባ ባለመሆኑ የኦዲት ስራው እንዲሳካ
መተግበር አለባቸው።
አመንቴ መቻሉ
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር
ታህሳስ/2016 ዓ.ም
