ከዋና ኦዲተር ጋር የተደረገ ጋዜጣዊ ቃለ-መጠይቅ
ጋዜጠኛዉ፡- ኦዲት ምንድን ነዉ? ዋና ኦዲተር፡- ኦዲት ማለት የአንድ ተቋም/ድርጅት የሀሳብ መግለጫዎች ፣የሂሳብ መዛግብት፣ መረጃዎች እንዲሁም የስራ ክንዉኖችን መመርመር፣መገምገምና መተንተን ማለት ነዉ፡፡እነዚህ ግምገማዎችና ትንተናዎችን ማካሄድ ብቻ ሳይሆን የተገኘዉ ዉጤት ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለተጠቃሚዉ አካል የኦዲት አስተያየት ማቅረብ ነዉ፡፡ ኦዲት በገለልተኛነት መካሄድ አለበት ካልሆነ ግን ኦዲት ዉጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ገለልተኛ ማለት ደግሞ ከማንኛዉም ህሊናዊና ቁሳዊ እንዲሁም የውጭ …